የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለሀ? በፊትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥
ዘፍጥረት 32:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የላከው የአገልጋይህ የያዕቆብ ነው፤ እርሱም ደግሞ እነሆ ከኋላችን ተከትሎናል’ በለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የላከው የባርያህ የያዕቆብ ነው፥ እርሱም ደግሞ እነሆ ከኋላችን ነው’ በለው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እነዚህ ከብቶች የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ እርሱ እነዚህን የላከው ለጌታዬ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነው፤ እነሆ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ ብላችሁ ንገሩት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ አንተ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደደው የባሪያህ የያዕቆብ ነው እርሱም ደግሞ እነሆ ከኍላችን ነው በለው። |
የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለሀ? በፊትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥
እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን፥ በፊቱ የሚሄዱትንና መንጋውን የሚነዱትን ሁሉ እንዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወንድሜ ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት፤