ዛሬ በጎችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለበትን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር ያለበትን ለይልኝ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።
ዘፍጥረት 31:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ፤ ነጫጮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫጮችን ወለዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ’ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ዝንጉርጉሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጉርጉሮችን ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ቢለኝ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ ወለዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባ ‘ዝንጒርጒሮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ዝንጒርጒር ወለዱ፤ ደግሞም ‘ሽመልመሌ መሳዮቹ ሁሉ ለአንተ ደመወዝ ይሁኑ’ ባለኝ ጊዜ፥ መንጋዎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮች ወለዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመወዝህ ዝንጕርጕሮች ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ ሽመልመሌ መሳዮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮችን ወለዱ። |
ዛሬ በጎችህ ሁሉ ይለፉ፤ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለበትን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር ያለበትን ለይልኝ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።