ዘፍጥረት 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቼም ባለኝ ዐቅም አባታችሁን ማገልገሌ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ባለኝ ጉልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጒልበቴን ሳልቈጥብ በትጋት አባታችሁን እንዳገለገልኩ እናንተም ታውቃላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። |
ያዕቆብም አለው፥ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብቶችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታውቅምን? ጥቂት ሆነው አግኝቻቸዋለሁና፤
አባታችሁ ግን አሳዘነኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግዚአብሔር ግን ክፉን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።