ያዕቆብም ወንድሞቹን፥ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ።
ዘፍጥረት 31:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “ይህች የድንጋይ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ትሁን” አለው። ላባም “ወግረ ስምዕ” ብሎ ጠራት፤ ያዕቆብም እንዲሁ አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም “ይጋር ሠሀዱታ” ብሎ ጠራት፥ ያዕቆብም “ገለዓድ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም ይጋርሣሀዱታ ብሎ ጠራት፤ ያዕቆብም ገለዓድ ብሎ ሰየማት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ይጋር ሠሀዱታ ብሎ ጠራት ያዕቆብም ገለዓድ አላት። |
ያዕቆብም ወንድሞቹን፥ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ።
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ፥ የኀጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።
ኢያሱም መሠዊያውን “የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ምስክር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆነ ይህ በመካከላቸው ምስክር ነውና።