ዘፍጥረት 30:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎቹም መጥተው በጠጡ ጊዜ ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር፥ ነቍጣም ያለበትን በበትሮቹ አምሳል ፀነሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትሮቹን ፊት ለፊት እያዩ ይሳረሩ ነበር፤ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ የጣለባቸውንም ግልገሎች ወለዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፥ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጉርጉር ነቁጣም ያለበቱን ወለዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዱላዎቹ ፊት ለፊት ፍትወት እየተሰማቸው ይጐመዡ ነበር፤ ስለዚህ ሸመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ የሆኑ ግልገሎችን ወለዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀውታቸው የተነሣ ፀነሱ፤ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበቱን ወለዱ። |
ያዕቆብም ተባት በጎችንና እንስት በጎችን ለይቶ ነጭና ሐመደ ክቦ በሆኑ አውራዎች ፊት አቆማቸው፤ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው። ከላባ በጎች ጋርም አልጨመራቸውም።
የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መዋረዴንና የእጆችን ድካም አየ፤ ትናንትም ገሠጸህ።”
ደመወዝህ ዝንጕርጕሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ፤ ነጫጮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫጮችን ወለዱ።