ዘፍጥረት 30:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም አለው፥ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብቶችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታውቅምን? ጥቂት ሆነው አግኝቻቸዋለሁና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም እንዲህ አለው፤ “መቼም እንዴት እንዳገለገልሁህ፣ ከብቶችህ በእኔ ጥበቃ ምን ያህል እንደ ተመቻቸው አንተ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም እንዲህ አለው “እንዴት እንዳገለገልኩህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደ ረባልህ አንተ ታውቃለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለው፦ እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ። |