ዘፍጥረት 30:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመወዝህን ንገረኝ፤ እርሱንም እሰጥሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቅስ ይገባኛል የምትለውን ደመወዝ ንገረኝና እከፍልሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ደመወዝህን ንገረኝ፥ እርሱንም እሰጥሃለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትፈልገውን ደመወዝ ልክ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመወዝህን ንገረኝ፥ እርሱንም እሰጥሃለሁ አለ። |
ለአንተ ቤት የተገዛሁልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
አባታችሁ ግን አሳዘነኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግዚአብሔር ግን ክፉን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።