ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልትቀበለው ወጣች፤ እንዲህም አለችው፥ “እኔ ዘንድ ታድራለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተስማምቼሃለሁና።”
ዘፍጥረት 30:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር አደረ። እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰችም፤ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ዐምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ስለዚህ ፀነሰችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስትኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። |
ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልትቀበለው ወጣች፤ እንዲህም አለችው፥ “እኔ ዘንድ ታድራለህ፤ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተስማምቼሃለሁና።”
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
መልአኩም እንዲህ አለው፥ “ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቶአልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፥ “ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።