ዘፍጥረት 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ፥ “አዳም፥ ወዴት አለህ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ግን አዳምን ተጣርቶ፣ “የት ነህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም አዳምን ጠርቶ፦ “ወዴት ነህ?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠርቶ “የት ነው ያለኸው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ ወዴት ነህ? አለው። |
የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጂያለሽ?” አላት። እርስዋም፥ “እኔ ከእመቤቴ ከሦራ ፊት እኰበልላለሁ” አለች።
እግዚአብሔርም ቃየልን አለው፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየልም አለ፥ “አላውቅም፤ በውኑ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?”
ከዚህም በኋላ ገብቶ፥ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “እኔ አገልጋይህ ወዴትም አልሄድሁም” አለ።