በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች።
ዘፍጥረት 29:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተሰበሰቡ ጊዜ እረኞች ድንጋይዋን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፤ ድንጋይዋንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንጎቹ ሁሉ በጕድጓዱ አጠገብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ፣ እረኞች ድንጋዩን ያንከባልሉና በጎቹን ውሃ ያጠጣሉ፤ ከዚያም ድንጋዩን በቦታው መልሰው የጕድጓዱን አፍ ይገጥሙታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፥ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጉድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጒድጓዱ ውሃ ያጠጡአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩን መልሰው በጒድጓዱ አፍ ላይ ይከድኑታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር። |
በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች።
እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።”
በብዙዎች ደስተኞች መካከል መሰንቆን ምቱ፤ በዚያ ለእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራን፥ በእስራኤልም ውስጥ ጽድቅንና ኀይልን ያቀርባሉ። ያንጊዜም የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማዎቹ ወረዱ።