La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዔሳ​ውም ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብን እንደ ባረ​ከው በአየ ጊዜ ከዚ​ያም ሚስ​ትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለቱ የሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ላከው፥ በባ​ረ​ከ​ውም ጊዜ፥ “ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አታ​ግባ” ብሎ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዔሳው፣ ይሥሐቅ ያዕቆብን መርቆ ሚስት እንዲያገባ ወደ ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ እንደ ላከውና በባረከውም ጊዜ “ከነዓናዊት ሴት አታግባ” ብሎ ትእዛዝ እንደ ሰጠው ሰማ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዔሳውም ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ ባረከው ባየ ጊዜ፥ ከዚያም ሚስትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለት ወንዞች መካካል እንደ ላከው፥ በባረከውም ጊዜ፦ ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ ብሎ እንዳዘዘው፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ መረቀውና ሚስት እንዲፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደ ላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው፦ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ” ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዔሳውም ይስሐቅ ያዕቆብ እንደ ባረከው ባየ ጊዜ ከዚይም ሚስትም ያገባ ዘንድ ወደ ሁለት ወንዞች መካካል እንደ ሰደደው፥ በባረከውም ጊዜ፦ ከከነዓን ሴቶች ልጆች ሚስትን አታግባ ብሎ እንዳዘዘው፥

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 28:6
4 Referencias Cruzadas  

ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”


ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን ጠራው፤ ባረ​ከ​ውም፥ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዘው፥ “ከከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አታ​ግባ፤


ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባ​ቱ​ንና የእ​ና​ቱን ቃል ሰምቶ ወደ ሁለቱ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ሄደ፥