ያዕቆብም እናቱን ርብቃን፥ “እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጕራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስላሳ ነኝ፤
ያዕቆብም እናቱን ርብቃን እንዲህ አላት፤ “ወንድሜ ዔሳው ሰውነቱ ጠጕራም ነው፤ የእኔ ገላ ግን ለስላሳ ነው።
ያዕቆብም ርብቃን እናቱን አላት፦ “እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጉራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስላሳ ነኝ፥
ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን “የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጒራም ነው፤ የእኔ ገላ ግን ምንም ጠጒር የሌለው ለስላሳ ነው፤
ያዕቆብም ርብቃን እናቱን አላት፦ እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጕራ፥ ሰው ነው እኔ ግን ለስላሳ ነኝ አባቴ ቢዳስሰኝ
የበኵር ልጅዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌረዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለንተናውም ጠጕራም ነበር፤ ስሙንም ዔሳው ብላ ጠራችው።
ለአባትህም ሳይሞት እንዲባርክህ፥ ይበላ ዘንድ ትወስድለታለህ።”
እርሱም አላወቀውም ነበር፤ እጆቹ እንደ ወንድሙ እንደ ዔሳው እጆች ጠጕራም ነበሩና፤ ይስሐቅም ባረከው ።