በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
ዘፍጥረት 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌራራ እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚያችንም ጕድጓድ ስም “ዐዘቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነርሱ በድለውታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌራራ እረኞች ግን፣ “ውሃው የእኛ ነው” በማለት ከይሥሐቅ እረኞች ጋራ ጠብ አነሡ፤ ከዚህ የተነሣ ይሥሐቅ ያን የውሃ ጕድጓድ ኤሴቅ ብሎ ጠራው፤ በጕድጓዱ ምክንያት ተጣልተውታልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌራራ አገር እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፦ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተከራከሩ፥ የዚያችንም ጉድጓድ ስም “ኤሴቅ” ብሎ ጠራት፥ ለእርሷ ሲሉ ተጣልተዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገራር እረኞች ግን “ይህ ውሃ የእኛ ነው” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ። በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጒድጓዱን “ዔሤቅ” ብሎ ሰየመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌራራ አገር እረኞች ለይስሐቅ እረኞች ጋር፦ ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ፤ የዚይችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና። |
በአብራምና በሎጥ መንጎች ጠባቆች መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐረብ በኩል በጌሤም እንድትቀመጡ እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴንነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን” በሉት።