ዘፍጥረት 25:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብም የምስር ንፍሮ ቀቀለችለት፤ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ሳለ ዔሳው እጅግ ተርቦ ከዱር መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ ሲሠራ፥ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ |
ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው።
አንዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በምድረ በዳውም የወይን ቦታ አገኘ፤ ከዚያም የምድር ቅጠላ ቅጠል ሰብሰበ፤ ልብሱንም ሞላ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ አበሰለውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።
አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፣ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።
ከሕዝቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባትህ፦ ዛሬ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን መሐላ አምሎአቸዋል” አለው፤ ሕዝቡም ደከሙ።