ስለ ይስማኤልም እነሆ፥ ሰምቼሃለሁ፤ እባርከዋለሁ፤ አበዛዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፤ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
ዘፍጥረት 25:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ የእስማኤል ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም በኖሩባቸውና በሰፈሩባቸው ቦታዎች የዐሥራ ሁለት ነገድ አለቆች ስሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይኸው ነው፥ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለዐሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰደራቸው ይኸው ነው በየወገናቸውም አሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። |
ስለ ይስማኤልም እነሆ፥ ሰምቼሃለሁ፤ እባርከዋለሁ፤ አበዛዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፤ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ።
ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ።