ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ ሦርያ ወንዞች መካከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
ዘፍጥረት 24:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውም በጌታው በአብርሃም እጅ ላይ እጁን አደረገ፤ ስለዚሁም ነገር ማለለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም አገልጋዩ እጁን ከጌታው ከአብርሃም ጭን በታች አድርጎ ስለዚህ ጕዳይ ማለለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሌውም ከጌታው ከአብርሃም ጭን በታች እጁን አደረገ ስለዚሁም ነገር ማለለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጒልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈጽም በመሐላ ቃል ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውም ከጌታው ለአብርሃም ጭን በታች እጁን አደረገ ስለዚህም ነገር ማለለት። |
ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነሥቶም ወደ ሦርያ ወንዞች መካከል ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።