እርሱም አለኝ፦ አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል። መንገድህንም ያቀናል፤ ለልጄም ከወገኖች ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፤
ዘፍጥረት 24:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኝ ሳለ አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እንድመለስ አሰናብቱኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፥ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን “እባካችሁ አታቈዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብዬ ወደ ጌታዬ ልመለስ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው። |
እርሱም አለኝ፦ አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል። መንገድህንም ያቀናል፤ ለልጄም ከወገኖች ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፤
ከዚህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ያሉትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚያም አደሩ፤ በማለዳም ተነሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።
የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንብበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል፤ አስተዋይም ትሆናለህ።