ዘፍጥረት 24:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጥናም እንስራዋን ከትከሻዋ አወረደችና፥ “አንተ ጠጣ፤ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ” አለችኝ፤ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎችንም ደግሞ አጠጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሷም ፈጥና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ፣ ‘ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣለሁ’ አለች። እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቹንም አጠጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጥናም እንስራዋን ከጫንቃዋ አወረደችና፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህንም ደግሞ አጠጣለሁ’ አለች፥ እኔም ጠጣሁ፥ ግመሎቼንም ደግሞ አጠጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እንስራዋን በፍጥነት ከትከሻዋ አወረደችና ዘንበል አድርጋ ‘እሺ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ’ አለችኝ፤ ስለዚህ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቼንም አጠጣችልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጥናም እንስራዋን ከጫንቃዋ አወረደችና፦ አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህንም ደግሞ አጠጣለሁ አለች፤ እኔም ጠጣሁ፥ ግመሎቼንም ደግሞ አጠጣች። |