እርስዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ለባሪያዉ ለይስሐቅ ያዘጋጃት ሚስት እርስዋ ትሁን። በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ዘፍጥረት 24:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እኔ በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆችም ውኃን ሊቀዱ ይወጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ ስላት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ በምንጩ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ ውሃ ልትቀዳ የምትመጣውን ኮረዳ፣ “ከእንስራሽ ውሃ አጠጪኝ” ስላት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥’ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም ቆንጆ፦ ‘ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ’ ስላት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ በዚህ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ አንዲት ልጃገረድ ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፥ እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ’ ብዬ እጠይቃታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፤ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም ቆንጆ፦ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ ስላት |
እርስዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ለባሪያዉ ለይስሐቅ ያዘጋጃት ሚስት እርስዋ ትሁን። በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”