ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው።
ዘፍጥረት 24:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይበላም ዘንድ እንጀራን አቀረቡለት፤ እርሱ ግን “ነገሬን እስክናገር ደረስ አልበላም” አለ። እነርሱም “ተናገር” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰውየውም ማእድ ቀረበለት፤ እርሱ ግን፣ “የመጣሁበትን ጕዳይ ሳልናገር እህል አልቀምስም” አለ። ላባም፣ “ዕሺ፤ ተናገር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብልንም በፊቱ አቀረበለት፥ እርሱ ግን፦ “ነገሬን እስክናገር ድረስ አልበላም” አለ። እርሱም፦ “ተናገር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገበታ በቀረበ ጊዜ ሰውየው “የተላክሁበትን ጉዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም” አለ። ላባም “ይሁን ተናገር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብልንም በፊቱ አቀረበለት፤ እርሱ ግን፦ ነገሬን እስክናገር ድረስ አልበላም አለ። |
ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”
የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ነገር ግን በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የሚያምኑና የተወደዱ ስለ ሆኑ፥ ከፊት ይልቅ ያገልግሉ።