ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሰውዬው አንድ አንድ ወቄት የሚመዝን የወርቅ ጉትቻ፥ ለእጆችዋም ዐሥር ወቄት የሚመዝን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፤
ዘፍጥረት 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠርቶም እንዲህ አላት፥ “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? በአባትሽ ቤት የምናድርበት ስፍራ እንዳለ እስኪ ንገሪኝ፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለመሆኑ አንቺ የማን ልጅ ነሽ? በአባትሽ ቤት የምናድርበት ስፍራ ይገኝ እንደ ሆነ፣ እባክሽ ንገሪኝ” ብሎ ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አላት፦ “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? እስኪ ንገሪኝ፥ በአባትሽ ቤት የምናድርበት ስፍራ ይገኛልን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የማን ልጅ ነሽ? እስቲ እባክሽ ንገሪኝ፤ ለእኔና አብረውኝ ላሉት ሰዎች ማደሪያ የሚሆን ስፍራ በአባትሽ ቤት ይገኛልን?” ብሎ ጠየቃት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህንም አላት፦ አንቺ የማን ልጅ ነሽ? እስኪ ንገሪኝ በአባትሽ ቤት የምናድርበት ስፍራ ይገኛልን? |
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ሰውዬው አንድ አንድ ወቄት የሚመዝን የወርቅ ጉትቻ፥ ለእጆችዋም ዐሥር ወቄት የሚመዝን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፤
እኔም “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ንገሪኝ” ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም፥ “ሚልካ የወለደችለት የናኮር ልጅ የባቱኤል ልጅ ነኝ” አለችኝ፤