አብርሃምም በግንባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በልቡም እንዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወልዳለሁን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
ዘፍጥረት 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ሣራ “በእርጅናዋ የወለደችውን ሕፃን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው?” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “ለመሆኑ፣ ‘ሣራ ልጆች ታጠባለች’ ብሎ ለአብርሃም ማን ተናግሮት ያውቅ ነበር? ይኸው በስተርጅናው ወንድ ልጅ ወለድሁለት” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ “ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥላም “ ‘ሣራ ለአብርሃም ልጅ ወልዳ ታጠባለች’ ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር? አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድኩለት” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፥ ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና አለች። |
አብርሃምም በግንባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በልቡም እንዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወልዳለሁን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?”
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ሣራን ለብቻዋ በልብዋ ምን አሳቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእውነትስ እወልዳለሁን? ጌታዬም አርጅትዋል እነሆ፥ እኔም አርጅቻለሁ ብላለችና።
የቴቄምናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌንባትን ለአዴር ወለደችለት፤ ቴቄምናስም በፈርዖን ልጆች መካከል አሳደገችው፤ ጌንባትም በፈርዖን ልጆች መካከል ነበረ።
ልጄንም አጠባ ዘንድ በማለዳ ብነሣ፥ ያን የሞተውን ልጅ አገኘሁ፤ ነገር ግን ብርሃን በሆነ ጊዜ ተመለከትሁት፤ እነሆም፥ የወለድሁት ልጄ አልነበረም።”
አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም መበለት ነኝና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?” ትያለሽ።
ከቶ እንዲህ ያለ ነገርን ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገርን ማን አይቶአል? በውኑ ሀገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።
በያዕቆብ ላይ ጥንቆላ የለም፤ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በየጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል፦ እግዚአብሔር ምን አደረገ? ይባላል።
ብዙ ልዩ ልዩ የሆነች የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤