La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 19:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሎ​ጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአ​ባ​ታ​ቸው ፀነሱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሁለቱም የሎጥ ሴት ልጆች ከአባታቸው አረገዙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ሁኔታ ሁለቱም የሎጥ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 19:36
9 Referencias Cruzadas  

አባ​ታ​ቸ​ው​ንም በዚ​ያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠ​ጡት፤ ታና​ሺ​ቱም ገብታ ከአ​ባቷ ጋር ተኛች፤ እር​ሱም ስት​ተ​ኛም ስት​ነ​ሣም አላ​ወ​ቀም።


ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው።


እነሆ፥ ወን​ድን ያላ​ወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነ​ር​ሱን ላው​ጣ​ላ​ችሁ፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁም አድ​ር​ጉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታ​ድ​ርጉ፤ እነ​ርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብ​ተ​ዋ​ልና።”


ኅፍረተ ሥጋውን ለማየት ባልንጀራውን ለሚያጠጣ፥ ክፉንም ለሚጨምርበት፥ ለሚያሰክረውም ወዮለት!


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው።


አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።


ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።