La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሣራን ለብ​ቻዋ በል​ብዋ ምን አሳ​ቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእ​ው​ነ​ትስ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ጌታ​ዬም አር​ጅ​ት​ዋል እነሆ፥ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ ብላ​ለ​ችና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሣራ፣ ‘ካረጀሁ በኋላ ልጅ እንዴት አድርጌ እወልዳለሁ’ ስትል ለምን ሣቀች?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም አብርሃምን “ሣራ ‘እንደዚህ ካረጀሁ በኋላ ልጅ መውለድ እችላለሁን’ በማለት ስለምን ሳቀች?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም አብርሃምም አለው፤ ካረጀሁ በኍላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 18:13
5 Referencias Cruzadas  

ሣራም ለብ​ቻዋ በል​ብዋ እን​ዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታ​ዬም ፈጽሞ ሽም​ግ​ሎ​አል።”


በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”


ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች።


ደግ​ሞም ሣራ “በእ​ር​ጅ​ናዋ የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን እን​ድ​ታ​ጠባ ለአ​ብ​ር​ሃም ማን በነ​ገ​ረው?” አለች።


የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።