La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም፥ “ወደ እመ​ቤ​ትሽ ተመ​ለሺ፤ ከእ​ጅ​ዋም በታች ራስ​ሽን ዝቅ አድ​ርጊ” አላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለርሷም ተገዥላት” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእግዚአብሔር መልአክም፦ “ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ” አላት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መልአኩም “ወደ እመቤትሽ ተመለሽና አገልግያት” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔር መልአክም፥ ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ አላት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 16:9
9 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም “ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እስ​ከ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ድረስ ዘር​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፥” አላት።


አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይሽ በእ​ጅሽ ናት፤ እንደ ወደ​ድሽ አድ​ር​ጊ​ባት” አላት። ሦራም አጋ​ርን አሠ​ቃ​የ​ቻት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ኰበ​ለ​ለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ለባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ።


ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።