ዘፍጥረት 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይም በገባ ጊዜ በአብራም ድንጋጤ መጣበት፤ እነሆም፥ የሚያስፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ ልትገባ ስትል አብራም እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማ መጣበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፥ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት እየተቃረበ ሲሄድ አብራምን ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እነሆ፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ መጣበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት፤ እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት፤ |
እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣ፤ አንቀላፋም ፤ ከጎኑም አጥንቶች አንድ አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ መላው።
ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፤ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና በዚያ አደረ፤ ከዚያም ስፍራ ድንጋዮች አንድ ድንጋይ አነሣ፤ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።
ስሙ አውጤክስ የሚባል አንድ ጐልማሳ ልጅም በመስኮት በኩል ተቀምጦ ሳለ ከባድ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ትምህርቱን ባስረዘመ ጊዜ ያ ጐልማሳ ከእንቅልፉ ብዛት የተነሣ ከተኛበት ከሦስተኛው ፎቅ ወደ ታች ወደቀ፤ ሬሳውንም አነሡት።
ዳዊትም በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውኃውን መንቀል ወሰደ፤ ወደ ቤታቸውም ተመለሱ። ማንም ያየ አልነበረም፤ ያወቃቸውም ማንም አልነበረም፤ የነቃም ማንም አልነበረም፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ እንቅልፍ ወድቆባቸው ነበርና ሁሉ ተኝተው ነበር።