የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል።
ዘፍጥረት 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሲባዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተባለች የባላቅ ንጉሥም ወጡ፤ እነዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሰዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የስቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ ሰራዊታቸውን አስተባበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፥ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሰዶም፥ የገሞራ፥ የአዳማ፥ የጸቦይምና የቤላዕ ነገሥታት ሠራዊታቸውን በሲዲም ሸለቆ አሰልፈው ተዋጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፤ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፤ |
የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል።
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ።
ከኤላም ንጉሥ ከኮሎዶጎሞር፥ ከአሕዛብ ንጉሥ ከቴሮጋል፥ ከሰናዖር ንጉሥ ከአሜሮፌል፥ ከእላሳር ንጉሥ ከአርዮክ ጋር ተጋጠሙ። እነዚህ አራቱ ነገሥታት ከአምስቱ ነገሥታት ጋር ተዋጉ።
እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት፤ እርስዋም ትንሽ ናት፤ ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰውነቴም ከዳነች ትንሽ አይደለችም፤”
እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።