Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 14:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም የሰዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የስቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት በሲዲም ሸለቆ ሰራዊታቸውን አስተባበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፥ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ የሰዶም፥ የገሞራ፥ የአዳማ፥ የጸቦይምና የቤላዕ ነገሥታት ሠራዊታቸውን በሲዲም ሸለቆ አሰልፈው ተዋጉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሰቦይም ንጉሥ፥ ዞዓር የተባለች የቤላ ንጉሥም ወጡ፤ እነዚህ ሁሉ በሲዲም ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 14:8
8 Referencias Cruzadas  

የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።


ሎጥ ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፣ የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ እንደ እግዚአብሔር ገነት፣ በዞዓር አቅጣጫ እንዳለው እንደ ግብጽ ምድር ውሃማ ቦታ ሆኖ አገኘው። እንዲህም የነበረው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነው።


በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጕድጓዶች ስለ ነበሩ የሰዶምና የገሞራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጕድጓዶች ውስጥ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራሮች ሸሹ።


እነዚህ ዐምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው።


እነሆ፤ ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ የሆነች ትንሽ ከተማ አለች፤ ወደ እርሷ ልሽሽ፤ በጣም ትንሽ አይደለችም እንዴ? ወደዚያ ብሸሽ እኮ ሕይወቴ ትተርፋለች።”


አንተ እዚያ እስክትደርስ ድረስ አንዳች ማድረግ ስለማልችል ቶሎ ብለህ ወደዚያ ሽሽ።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ዞዓር ተባለ።


“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos