ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
ዘፍጥረት 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰዶምን ፈረሶች ሁሉ አስመለሰ፤ ደግሞም የወንድሙን ልጅ ሎጥንና ንብረቱን፥ ሴቶችንና ሕዝቡንም አስመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ የወንድሙን ልጅ ሎጥን፣ ንብረቱን እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎቹን ምርኮኞች አስመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብቱንም ሁሉ አስመለሰ፥ ደግሞም ወንድሙን ሎጥንና ከብቶቹን ሴቶችንና ሕዝቡን ደግሞ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተወሰደውንም ምርኮ ሁሉ መልሶ አመጣ፤ እንዲሁም የወንድሙን ልጅ ሎጥን ከነሀብቱ መልሶ አመጣ፤ ከእነርሱም ጋር ሴቶችና ሌሎች እስረኞች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብቱንም ሁሉ አስመለሰ፥ ደግሞም ወንድሙን ሎጥንና ከብቶቹን ሴቶችንና ሕዝቡን ደግሞ መለሰ። |
ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ ቡሩክም ትሆናለህ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤
አብራምም የወንድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ ወገኖቹንና ቤተሰቦቹን ሁሉ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከትሎ አሳደዳቸው።
ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፤ የፈርዖን ሎሌዎችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፤
ከምሥራቅ ጽድቅን ያስነሣ፥ ይከተለውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? በአሕዛብና በነገሥታት ፊት ድንጋጤን ያመጣል። ጦሮቻቸውን በምድር ያስጥላቸዋል፤ ቀስቶቻቸውም እንደ ገለባ ይረግፋሉ።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።