አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅጣጫ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም ኖረ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።
ዘፍጥረት 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም ከግብፅ ወጣ፤ እርሱና ሚስቱ፥ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም ሚስቱንና ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከግብጽ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም ዐብሮት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም ከግብጽ ወጣ፥ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም ሚስቱንና ያለውን ሀብት ሁሉ ይዞ ከግብጽ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። |
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅጣጫ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም ኖረ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።
አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
ወደ ጤሮስም ምሽግ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፤ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣል፤ የዮሴፍም ልጆች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀመጣሉ።
አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው።