ዘፍጥረት 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኀያል መሆን ጀመረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኵሽ የናምሩድን አባት ነበረ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኀያል ጦረኛ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኩሽም ናምሩድን ወለደ፥ እርሱም በምድር ላይ ቀዳሚው ኃያል ጦረኛ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኩሽ በዓለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረውን ናምሩድን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሽም ናምሩድን ወለደ እርሱም በምድር ላይ ኃያክክ መሆንን ጀመረ። |
በዚያም የሚያበራ ዕንቍና የሚያብረቀርቅ ዕንቍ አለ። የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፤
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል። ፈጣኖች መልእክተኞች ወደ ረዥምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቈረጡና የተረገጡ ሕዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሀገር ይኖራሉ።
የአሦርንም አገር በሰይፍ፥ የናምሩድንም አገር በመግቢያው ውስጥ ያፈርሳሉ፥ አሦራዊውም ወደ አገራችን በገባ ጊዜ፥ ዳርቾቻችንንም በረገጠ ጊዜ እርሱ ይታደገናል።