ገላትያ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም የሚያምኑ ከአመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በእምነት የሆኑት፣ የእምነት ሰው ከሆነው ከአብርሃም ጋራ ቡሩካን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የሚያምኑት ከታመነው ከአብርሃም ጋር ተባርከዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሚያምኑ ሁሉ ከአመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ። |
ሳይገዘር እግዚአብሔር አብርሃምን በእምነት እንደ አጸደቀው በእርሱ ላይ ይታወቅ ዘንድ ግዝረትን የጽድቅ ማኅተም ትሆነው ዘንድ ምልክት አድርጎ ሰጠው። ሳይገዘሩ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብርሃም በእምነት እንደ ከበረ እነርሱም በእምነት እንደሚከብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዘሩ የሰጠው ተስፋ የታመነ ይሆን ዘንድ፥ የሚጸድቁ በእምነት እንጂ የኦሪትን ሥራ በመፈጸም ብቻ እንዳይደለ ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጽድቅን በእምነት አደረገ።
ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለውን፥ ሊያስነሣንና ሊያጸድቀን የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ በአስነሣው ስለምናምን ስለ እናም ነው እንጂ።
እኛ በክርስቶስ አምነን የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ እንድናገኝ የአብርሃም በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አሕዛብ ይመለስ ዘንድ።