አሁንም ከአንተ ዘንድ የወጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ መጡ ጌታቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመፀኛዪቱንና እጅግም የከፋችቱን ከተማ ይሠራሉ፤ ቅጥርዋንም ያድሳሉ፤ መሠረቷንም ጠገኑ።
ዕዝራ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያንም ሽማግሌዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘዛችሁ? የምትሠሩበትንስ ሥልጣን ማን ሰጣችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም መሪዎቹን፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ይህንም ውቅር ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ብለን ጠየቅናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም ሽማግሌዎቹን፦ ‘ይህን ቤት እንድትሠሩ፥ ይህንንም ቅጥር እንድታድሱ ማን አዘዛችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛም የሕዝቡን መሪዎች ‘ይህን ቤተ መቅደስ እንደገና መልሳችሁ ለመሥራትና ቅጽሮቹንም ለማደስ ማን ፈቀደላችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያንም ሽማግሌዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንስ ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው?’ ብለን ጠየቅናቸው። |
አሁንም ከአንተ ዘንድ የወጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ መጡ ጌታቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመፀኛዪቱንና እጅግም የከፋችቱን ከተማ ይሠራሉ፤ ቅጥርዋንም ያድሳሉ፤ መሠረቷንም ጠገኑ።
ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በጥሩ ድንጋይ ይሠራል፤ በቅጥሩም ውስጥ ልዩ እንጨት ይደረጋል፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል።