La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ላይ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን አወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሆኖም ግን አስማተኞቹ በድብቅ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር ሠሩ፤ እነርሱም በግብጽ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንቁራሪቶቹን ከአንተ ከቤቶችህም ከአገልጋዮችህም ከሕዝብህም ያርቃል፤ በዓባይ ወንዝ ብቻ ይቀራሉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን አስማተኞችም እንደዚሁ በአስማታቸው ተጠቅመው ጓጒንቸሮች በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ አደረጉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጠንቍዮችም በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በግብፅም አገር ላይ ጓጕንቸሮችን አወጡ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 8:7
8 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ።


የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም።


የግ​ብፅ ጠን​ቋ​ዮ​ችም በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉም፤ ቅማ​ሉም በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ነበረ።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።


በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።