ግብፃውያንም ሁሉ ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ ዳር ውኃ ሊጠጡ ቈፈሩ።
ግብጻውያን ሁሉ የወንዙን ውሃ መጠጣት ባለመቻላቸው ውሃ ለማግኘት የአባይን ዳር ይዘው ጕድጓድ ቈፈሩ።
ግብጽም ሁሉ የዓባይ ወንዝ አካባቢውን ቆፈሩ የዓባይን ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉምና።
ግብጻውያን ከዐባይ ወንዝ ውሃ መጠጣት ስላልቻሉ የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት ከዐባይ ወንዝ ዳር ጒድጓድ ቈፈሩ።
ግብፃውያንም ሁሉ የወንዙን ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ አጠገብ ውኃ ሊጠጡ ቆፈሩ።
በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት አይችሉም።”
ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ በዚህም ሁሉ ልቡ አልተመለሰም።
እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።