በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ።
ዘፀአት 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት አይችሉም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለው ዓሣ ይሞታል፤ ወንዙ ይከረፋል፤ ግብጻውያንም ውሃውን መጠጣት አይችሉም።” ’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓባይ ወንዝ ያሉትም ዓሦች ይሞታሉ፥ የዓባይ ወንዝም ይገማል፤ ግብፃውያንም የዓባይን ወንዝ ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውስጡ ያሉ ዓሣዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ የዐባይ ውሃ በጣም ከመሽተቱ የተነሣ ግብጻውያን ከዚህ ወንዝ ውሃ ቀድተው መጠጣት አይችሉም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” |
በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ።
ነገር ግን በመካከላችሁ ያለውን እግዚአብሔርን ንቃችኋልና፥ በፊቱም፦ ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ብላችሁ አልቅሳችኋልና በአፍንጫችሁ እስኪወጣ መርዝም እስኪሆንባችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ።”
ሕዝቡም፥ “በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” ብለው እግዚአብሔርንና ሙሴንም አሙ። “እንጀራ የለም፤ ውኃም የለምና፥ ሰውነታችንም ይህን ጥቅም የሌለው እንጀራ ተጸየፈች” ብለው ተናገሩ።