ዘፀአት 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ የያዛትን በትር ጣለ፤ እባብም ሆነች። ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ዋጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትሮቻቸውን ወደ መሬት በጣሉአቸው ጊዜ ተለውጠው እባቦች ሆኑ፤ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ሁሉ ዋጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች። |
ጠንቋዮችም ቍስል ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤ ቍስል ጠንቋዮችንና ግብፃውያንን ሁሉ ይዞአቸው ነበርና።