በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።
ዘፀአት 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈርዖንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደርጉት እንደ ነበራችሁ እንደ ትናንትናውና እንደ ትናንትና በስቲያው የተቈጠረውን ጡብ ዛሬስ ስለምን አትጨርሱም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆች ይገርፉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥራው የቅርብ ኀላፊዎች ተደርገው በፈርዖን የባሪያ ተቈጣጣሪዎች የተመደቡት እስራኤላውያንም፣ “የትናንቱንም ሆነ የዛሬውን ሸክላ ሥራ ድርሻችሁን እንደ ቀድሞው ለምን አላሟላችሁም?” እየተባሉ ይጠየቁና ይገረፉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “የተወሰነላችሁን የጡብ ሥራ ትናንትናና ዛሬ ለምን እንደ ቀድሞው አልጨረሳችሁም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎች፥ የእስራኤላውያን ሠራተኞችን አለቆች “ቀድሞ ትሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ሠርታችሁ የማታስረክቡት ስለምንድነው?” እያሉ ይገርፉአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “ቀድሞ ታደርጉ እንደ ነበራችሁ ትናንትናና ዛሬ የተቆጠረውን ጡብ ስለ ምን አትጨርሱም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ። |
በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።
የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ “ለምን በአገልጋዮችህ እንዲህ ታደርጋለህ? ገለባ አይሰጡአቸውም፤ ጡቡንም ሥሩ ይሉአቸዋል፤
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአሦር የተነሣ አትፍራ፤ በበትር ይመቱሃልና፥ የግብፅንም መንገድ ታይ ዘንድ መቅሠፍቴን አመጣብሃለሁና።