ዘፀአት 40:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅብዐቱንም ዘይት ወስደህ ድንኳኑን፥ በውስጥዋም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፤ እርስዋንም ዕቃዋንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅድስትም ትሆናለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቅብዐ ዘይቱን ወስደህ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቅባ፤ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ቀድስ፤ የተቀደሰም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቅባቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን እና በእርሱ ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፥ እርሱን፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅዱስም ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚያም በኋላ ድንኳኑን ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር የቅባቱን ዘይት በመቀባት ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው፤ የተቀደሰም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅብዓቱንም ዘይት ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀባለህ፥ እርሱንም ዕቃውንም ሁሉ ትቀድሳለህ፤ ቅዱስም ይሆናል። |
የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኀይል መንፈስ፥ የዕውቀትና የእውነት መንፈስ ያርፍበታል።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
አንተ ልትጋርድ የተቀባህ ኪሩብ ነበርህ፤ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ፤ በእሳት ድንጋዮች መካከል ተመላለስህ።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ድንኳኑን ፈጽሞ በተከለባት፥ እርስዋንና ዕቃዋን ሁሉ በቀባና በቀደሰባት፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ በቀባና በቀደሰባት ቀን፥
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
እግዚአብሔር በአጽናናን በዚያ መጽናናት በመከራ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንችል ዘንድ ከመከራችን ሁሉ ያጽናናን እርሱ ይመስገን።