ዘፀአት 38:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሎጊያዎቹንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሠራ፤ በናስም ለበጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርተው በንሓስ ለበጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠራ፥ በነሐስም ለበጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠራ፥ በናስም ለበጣቸው። |
ይሸከሙባቸውም ዘንድ በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አገባ፤ ከሳንቃዎቹም ሠርቶ ክፍት አደረገው።
ከማይነቅዝ እንጨትም ታቦቱን ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረፅሁ፤ ወደ ተራራውም ወጣሁ፤ ሁለቱም ጽላት በእጄ ነበሩ፤