መሎጊያዎቹንም ከማይነቅዝ ዕንጨት አደረገ፤ በወርቅም ለበጣቸው።
መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ በወርቅም ለበጧቸው።
መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠራ፥ በወርቅም ለበጣቸው።
መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
መሎጊያዎቹንም ከግራር እንጨት አደረገ፥ በወርቅም ለበጣቸው።
የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቍርበት፥ ሰማያዊ ቀለም የገባ ቍርበት፥ የማይነቅዝ ዕንጨት፥
ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱም ጎን አደረጋቸው፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች መግቢያ ነበሩ።
የተቀደሰውንም የቅብዐቱን ዘይት፥ ጥሩውንም የጣፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ አደረገ።