ዘፀአት 37:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ፥ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላዩን፣ ጐኖቹን ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጧቸው፤ በዙሪያው የወርቅ ክፈፍ አበጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላዩን፥ የጎኑን ዙሪያ በሙሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጫፉን፥ አራት ጐኖቹንና ጒጦቹን ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ለበጠ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገበት። |
የዕጣን መሠዊያንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሠራ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፤ አራት ማዕዘን ነበር፤ ከፍታውም ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድነት የተሠሩ ነበሩ።
ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱም ጎን አደረጋቸው፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች መግቢያ ነበሩ።