በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች አድርግ።
ዘፀአት 37:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንደኛው ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዝዋ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋራ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች በአንዱ ቅርንጫፍ ላይ፣ ሦስቱ ደግሞ በሚቀጥለው ቅርንጫፍ ላይ ነበሩ፤ ከመቅረዙ ለወጡት ለስድስቱም ቅርንጫፎች ሁሉ እንዲሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስቱም ቅርንጫፎች እያንዳንዱ እንቡጥና ቀንበጥ ያላቸውን የለውዝ አበባዎችን የሚመስሉ ሦስት ሦስት ጌጠኛ የአበባ ወርድ ተስለውበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንደኛው ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ። |
በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች አድርግ።
በስተጎንዋ ስድስት ቅርንጫፎች ወጡላት፤ ሦስቱ የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በሁለተኛው ወገን ወጡ።