ሠራተኞችም ሠሩ፤ ሥራውም ሁሉ በእጃቸው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት እንደ ቀድሞው ሥራ መለሱ፤ አጽንተውም አቆሙት።
ዘፀአት 36:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዳቸው በሚሠሩት የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ መጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የመቅደሱን ሥራ ሁሉ ይሠሩ የነበሩ ጥበበኞች የሆኑ ባለሙያዎች ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሥራውን የሚያከናውኑት ጥበበኞች ሁሉ ሥራቸውን ትተው ወደ ሙሴ በመሄድ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቅደሱንም ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ የሚያደርጉትን ሥራ ትተው መጡ፥ |
ሠራተኞችም ሠሩ፤ ሥራውም ሁሉ በእጃቸው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት እንደ ቀድሞው ሥራ መለሱ፤ አጽንተውም አቆሙት።
እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?
እግዚአብሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠራቢዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠረት ጣልሁ፤ ሌላውም በእርሱ ላይ ያንጻል፤ እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።