ስምንት ሳንቆችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች በሁለቱም መጋጠሚያዎች ሁለት ሁለት እግሮች ይሆናሉ።
ዘፀአት 36:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምንት ሳንቆችና ዐሥራ ስድስቱ የብር እግሮቻቸው፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግሮች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ስምንት ወጋግራዎችና ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ሆነው ዐሥራ ስድስት የብር መቆሚያዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምንት ሳንቃዎች ነበሩ፥ የብር እግሮቻቸውም ዐሥራ ስድስት እግሮች ነበሩ፥ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እያንዳንዱ ተራዳ በሥሩ ሁለት እግሮች እንዲኖሩት በማድረግ ስምንት ተራዳዎችና ከብር የተሠሩ ዐሥራ ስድስት እግሮች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስቱ የብር እግሮቻቸው፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግሮች ነበሩ። |
ስምንት ሳንቆችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች በሁለቱም መጋጠሚያዎች ሁለት ሁለት እግሮች ይሆናሉ።