ዘፀአት 36:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኑም አንድ እንዲሆን ያጋጥሙት ዘንድ አምሳ የናስ መያዣዎችን ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳኑን አንድ ወጥ አድርጎ ለማያያዝም ዐምሳ የንሓስ ማያያዣዎችን ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳኑ አንድ ወጥ እንዲሆን የሚያጋጥሙበት አምሳ የነሐስ መያዣዎችን ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለቱም በኩል ያሉትን መጋረጃዎች አገጣጥመው አንድ መክደኛ ለማበጀት ኀምሳ የነሐስ መያዣዎችን ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንኳኑም አንድ እንዲሆን ያጋጥሙት ዘንድ አምሳ የናስ መያዣዎችን ሠሩ። |
ከተጋጠሙትም መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ።