ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
ዘፀአት 36:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚጋጠሙትም መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አደረጉ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተጋጥሞ ከተሰፋው መጋረጃ ጠርዝ ጫፍ ላይ ከሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አበጁ፤ ተጋጥሞ በተሰፋው በሌላው መጋረጃ ጫፍ ላይም ተመሳሳይ ነገር አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ በመጋጠሚያው ላይ የሰማያዊው ግምጃ ቀለበቶች አደረገ፤ ደግሞ በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በመጋጠሚያው ላይ እንዲሁ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተገጣጠሙት መጋረጃዎች በአንደኛው ክፍል ጠርዝ ላይ ከሰማያዊ ግምጃ የተሠሩ ቀለበቶችን አደረጉ፤ በሌላም በኩል ተገጣጥመው ከተሰፉት መጋረጃዎችም በአንደኛው ጠርዝ ላይ እንዲሁ አደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚጋጠሙትም መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አደረጉ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አደረጉ። |
ከሚጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ የሰማያዊውን ግምጃ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እንዲሁ አድርግ።
አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንዱን ከሌላው ጋር አጋጠሙ፤ አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው እንዲሁ አጋጠሙ።
አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አደረጉ፤ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አደረጉ፤ ቀለበቶቹ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት የሚተያዩ ነበሩ።