ቀይ ቀለምም የገባበት የአውራ በግ ቍርበት፥ የአቆስጣም ቍርበት፥ የማይነቅዝም ዕንጨት፤
ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ እንዲሁም የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤
ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፤
ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ የለፋ ቊርበት፥ የግራር እንጨት፥
ቀይም የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣም ቁርበት፥ የግራርም እንጨት፤
የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቍርበት፥ ሰማያዊ ቀለም የገባ ቍርበት፥ የማይነቅዝ ዕንጨት፥
ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአቆስጣ ቍርበት አድርግ።
ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ድርብ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፤
ለመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ሽቱን፥ ለማዕጠንት ዕጣንን፤