በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ዘፀአት 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምስክሩም ድንኳን በገቡ ጊዜ እንዳይሞቱ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠባሉ፤ ይህም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ለአሮንና ለትውልዶቹ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳይሞቱ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንዳይሞቱ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠቡ፤ ይህም እነርሱና ከእነርሱ በኋላ የሚነሡት ዘሮቻቸው ለዘለዓለም የሚጠብቁት ቋሚ ሥርዓት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳይሞቱም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘላለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል። |
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
ወደ ምስክሩ ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መሥዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል።