ዘፀአት 29:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንና ልጆቹም የአውራውን በግ ሥጋ፥ በመሶብም ያለውን እንጀራ በምስክሩ ድንኳን በር ይበሉታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንና ወንዶች ልጆቹ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ የአውራውን በግ ሥጋና በሌማት ያለውን ዳቦ ይብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንና ልጆቹ የአውራውን በግ ሥጋና በሌማት ያለውን ቂጣ በመገናኛው ድንኳን በር ሆነው ይበሉታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ሥጋ በመሶብ ውስጥ ተርፎ ከቀረው ቂጣ ጋር በቅዱሱ ድንኳኔ ደጃፍ ሆነው ይብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንና ልጆቹም የአውራውን በግ ሥጋ በሌማትም ያለውን እንጀራ በመገናኛው ድንኳን በር ይበሉታል። |
ለመክበራቸው እጆቻቸውን ይቀድሱ ዘንድ በተቀደሱበት በዚያ ቦታ ይብሉት፤ የባዕድ ልጅ ግን አይብላው፤ የተቀደሰ ነውና።
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው፥ “ሥጋውን በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በተቀደሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮንና ልጆቹ ይብሉት ብሎ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ በዚያ እርሱንና በቅድስናው መሶብ ያለውን እንጀራ ብሉ።